"ፍቅር ያሸንፋል" - በቴዲ አፍሮ Teddy's Afro New Single, "Love wins"

ዋሽቶ ለመኖር (አቤት)አልችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ:
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ገንዘብ ለማግኝት ብዬ አላጣም ስላም:
እኔ አላጣም ሰላም::

ይህ ዓለም ንዋይ ጭኖ ወርቁን በሙዳይ
ማርኮ ከረታት ነፍሴን ከሰጣት ጉዳይ:
ህሊና ሲያጣ ሰላም ወርቅ አልማዝ ሞልቶ
ሳይተኙ ማደር ሊሆን ከራስ ተጣልቶ::
ከእዚህ ሁሉ ቅጣት ይሻላል ማጣት
አስኮንኛት ነፍሴን አልሞላም ኪሴን::

ነፍሴ- እጅ እንዳትሰጪው ለኪሴ
ታጣይኛለሽ ከእራሴ::
ስላሜ እረፍት ያለብሽ በጌታ
ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ::

(አንገት ከሚሰበር
ባይበላስ ቢቀር::
ያሉት ከሚጠፋ
የወለዱት ይጥፋ::
ይሉኝታ ከማጣ
ዛሬ ገንዘብ ልጣ::
አስገምቼው ራሴን
አልሞላውም ኪሴን)2
(አልሞላውም ኪሴን)2
(ባዶ ላርገው ኪሴን)2
አልሞላውም ኪሴን) - ባዶ

ዋሽቶ ለመኖር (አቤት) አልችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ይሄን ለማግኘት ብዬ አላጣም ስላም
እኔ (አላጣም ሰላም)2::

የዓመል ነው እንጂ ደሀ የገንዘብ የለም
ሰው ባይኖር እይዋት ራሷ ባዶ ናት ዓለም
ገንዘብ ብቻ ነው ያለ የእዚህ ዓለም ደስታ
ዳግም ይሸጣል ስምዖን ቢመለስ ጌታ::
ለሰላሣ ዲናር
ሊያጣ ነፍስ ይማር
አስኮንኛት ነፍሴን
አልሞላም ኪሴን
ነፍሴ... እጅ እንዳትሰጪው ለኪሴ
ታጣይኛለሽ ከእራሴ
ሰላሜ እረፍት ያለብሽ በጌታ
ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ

(አንገት ከሚሰበር
ባይበላስ ቢቀር::
ያሉት ከሚጠፋ
የወለዱት ይጥፋ::
ይሉኝታ ከማጣ
ዛሬ ገንዘብ ልጣ::
አስገምቼው ራሴን
አልሞላውም ኪሴን::)2

(አልሞላውም ኪሴን::)2
(ባዶ ላርገው ኪሴን)2
(አልሞላውም ኪሴን::)2

Labels:

posted by Ethiounited Moderator at12:19 PM

0 Comments:

Post a Comment

<< Home